ቅዱስ አባ ጳውሊ ወ አባ እንጦንስ | Antony the Great and St Paul the first Hermit
HTML-код
- Опубликовано: 14 апр 2025
- ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††
††† ታላቁ ቅዱስ ጳውሊ ††† የካቲት ፪
ምንጭ፡- ዝክረ ቅዱሳን Saints Of The Orthodox Church (Facebook Page)
††† በቤተ ክርስቲያን አስተምሕሮ "ታላቁ /ዐቢይ/ THE GREAT" የሚል ስም የሚሰጣቸው አባቶች የተለዩ ናቸው። አንድም እጅግ ብዙ ትሩፋቶችን የሠሩ ናቸው። በሌላ በኩል ደግሞ በተመሳሳይ ስም ከሚጠሩ ሌሎች ቅዱሳን እንለይበታለን።
ገዳማዊ ሕይወት ጥንቱ ብሉይ ኪዳን ነው። በቀዳሚነትም በደብር ቅዱስ አካባቢ ይኖሩ የነበሩ ደቂቀ ሴት እንደ ጀመሩት ይታመናል። ሕይወቱ በጐላ በተረዳ መንገድ የታየው ግን በታላቁ ጻድቅ ሄኖክ ከዚያም በቅዱሱ ካህን መልከ ጼዴቅ አማካኝነት ነው።
ቀጥሎም እነ ቅዱስ ኤልያስ ነቢይ እነ ኤልሳዕ ደቀ መዝሙሩ ኑረውበታል። በሐዲስ ኪዳን ደግሞ ሙሉ ሕይወቱን በገዳም (በበርሃ) ያሳለፈው መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ቅድሚያውን ይይዛል።
ለስም አጠራሩ ስግደት ይሁንና መድኃኒታችን ክርስቶስ በገዳመ ቆረንቶስ ለአርባ ቀናት በትሕርምት ኑሮ ገዳማዊ ሕይወትን ቀድሷል፤ አስተምሯል። በዘመነ ስብከቱም ያድርባት የነበረችው የደብረ ዘይቷ በዓቱ (ኤሌዎን ዋሻ) በራሷ ለዚህ ሕይወት ትልቅ ማሳያ ናት።
ከጌታ ዕርገት በኋላም ክርስቲያኖቹ የዓለም ሁካታ ሲሰለቻቸው አንድም በንጹሕና በተሸከፈ ልቡና ለፈጣሪያቸው መገዛትን ሲሹ ከከተማ ወጣ እያሉ ይኖሩ እንደ ነበር የታሪክ መዛግብት ያሳያሉ። አኗኗራቸውም በቡድንም በነጠላም ሊሆን ይችላል። ዋናው ነገር ግን በጾምና በጸሎት መትጋታቸው ነው። ይህም ሲያያዝ እስከ ሦስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ደረሰ። በዚህ ዘመን ግን አባ ጳውሊ የሚባል ንጹሕ ክርስቲያን ይህንን ሕይወት ወደ ሌላ ደረጃ ከፍ አደረገው። ለሰማንያ ዓመታት ሰው ሳያይ ተጋድሎ "የባሕታውያን አባት" ተባለ። ደንብ ያለው ተባሕትዎም ጀመረ።
ይህ ከሆነ ከሃያ ዓመታት በኋላ ደግሞ አባ እንጦንስ የሚባሉ ደግ ክርስቲያን ይህንን ገዳማዊ ሕይወት በሌላ መንገድ አጣፈጡት። በቅዱስ ሚካኤል አመንኳሽነት ገዳማዊ ሕይወት በምንኩስና ተቃኘ። ስለዚህም አባ እንጦንስ የመነኮሳት አባት ተባሉ።
እርሳቸውም ሕይወቱን ለማስፋፋት ከተለያዩ አሕጉር ደቀ መዛሙርትን እየተቀበሉ አመንኩሰዋል። ቅዱሳን የአባ እንጦንስ ልጆችም ወደየ ሃገራቸው ተመልሰው ሕይወቱን በተግባር አሳይተው ገዳማዊነትን አስፋፍተዋል።
አንድ ቀን ቅዱስ እንጦንስ (የመነኮሳት ሁሉ አባት) እንዲህ ሲል አሰበ። "በውኑ በበርሃ ለበርካታ ዘመናት በመኖር ከእኔ የሚቀድም (የሚበልጥ) ሰው ይኖር ይሆን?"
ይህንን ሃሳቡን ገና ሳይጨርሰው ቅዱስ ሚካኤል ወደ እርሱ ዘንድ ደረሰ።
"እንጦንስ ሆይ! ከእኔ የሚቀድም የበርሃ ሰው ይኖር ይሆን ብለህ አስበሃል። በእርግጥም ከአንተ ሃያ ዓመታትን ቀድሞ ወደ በርሃ የገባ፣ በቅድስናው ፈጣሪውን ያስደሰተ፣ ዓለም ከነ ክብሯ የእግሩን መረገጫ ያህል እንኳ የማትመጥነው በጸሎቱና በምልጇው ዓለም የምትጠበቅለት ሞገስን የተሞላ አንድ ሰው በበርሃ ስላለ ሒድና ተመልከተው።" ብሎት ተሠወረው።
ቅዱስ እንጦንስም ከሰማው ነገር የተነሳ እየተደነቀ ተነሳ። እርሱ ካለበት በርሃ በራቀ መንገድም ለቀናት ተጉዞ አንድ በዓት (ዋሻ) በር ላይ ደረሰ። በበሩ አካባቢ የሰውና የአራዊት ኮቴ ተመልክቶ በሩን ጸፋ (ቆፈቆፈ)። በውስጥ ያለው አረጋዊ ሰው ግን ትልቅ ድንጋይ ገልብጦ በሩን አጠበቀው። ለሰማንያ ዓመታት ሰውን አይቶ አያውቅምና ሰይጣን ሊያታልለኝ መጥቷል ብሎ አስቧል። ቅዱስ እንጦንስ ግን "ኃሠሥኩ እርከብ ጐድጐድኩ ይትረኃው ሊተ - ሽቻለሁና ላግኝ፤ ደጅ መትቻለሁና ይከፈትልኝ።" ሲል አሰምቶ ተናገረ።
ቅዱሱ ገዳማዊም ሰው መሆኑን ሲያውቅ በሩን ከፈተለትና ወደ ዋሻው አስገባው። መንፈሳዊ ሰላምታንም ተለዋወጡ። ሲመሽም ቅዱስ እንጦንስ ሽማግሌውን ገዳማዊ "ስምህ ማን ነው?" ቢለው "ስሜን ካላወክ ለምን መጣህ?" ሲል መለሰለት።
ያን ጊዜ ቅዱስ እንጦንስ ቀና ብሎ ሰማይን ሲመለከት ምሥጢር ተገለጠለትና "ቅዱስ ጳውሊ ሆይ! ከአንተ ጋር ያገናኘኝ ፈጣሪ ይክበር፤ ይመስገን።" ሲል ፈጣሪውን ባረከ። ቅዱስ ጳውሊም መልሶ (በጸጋ አውቆት) "አባ እንጦንስ ሆይ! እንኳን ደህና መጣህ።" አለው። ሁለቱም ደስ ብሏቸው ፈጣሪያቸውን እያመሰገኑ ተጨዋወቱ።
ቤተ ክርስቲያን ለሁሉም ዓይነት የቅድስና ሕይወት የመጀመሪያ የምትላቸው አላት። ለምሳሌ፦
የመጀመሪያው ሐዋርያ ቅዱስ እንድርያስ፣
የመጀመሪያው ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስ፣
የመጀመሪያው ባሕታዊ (ገዳማዊ) ቅዱስ ጳውሊ እና የመጀመሪያው መነኮስ ቅዱስ እንጦንስን ማንሳት እንችላለን።
ቅዱስ ጳውሊ የተወለደው በሰሜናዊ ግብጽ በእስክንድርያ ከተማ ሲሆን ዘመኑም ሦስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ ነው። ወላጆቹ ባለጸጐች ነበሩ። ቅዱሱንና ታላቅ ወንድሙን አባ ጴጥሮስን ወልደዋል። ሁለቱ ክርስቲያን ወንድማማቾች ገና ወጣት ሳሉ ወላጆቻቸው ሞቱባቸው። ሃዘናቸውን ፈጽመው ሃብት ሲካፈሉ ግን መስማማት አልቻሉም።
ምክንያቱ ደግሞ ትልቁ ጴጥሮስ ደህና ደህናውን እቃ ወስዶ መናኛ መናኛውን ለትንሹ ለጳውሎስ (ጳውሊ) መስጠቱ ነበር። ስለዚህ ነገር ተካሰው ወደ ፍርድ ቤት ሲሔዱ ግን መንገድ ላይ አንድ ባለጸጋ ሙቶ ደረሱ።
ቆመው ሳሉም ቅዱስ መልአክ ሰው መስሎ ጳውሊን "ይህ ሰው ባለጸጋ ነው። በገንዘቡ የሰጠውን ፈጣሪ ሲበድልበት ኑሮ እነሆ ተሸኘ። በሰማይም አስጨናቂ ፍርድ ይጠብቀዋል።" ሲል ነገረው።
በዚያች ቅጽበት የወጣቱ ጳውሊ ሐሳብ ተለወጠ። ወደ ወንድሙ ተመልሶ "ወንድሜ ሆይ! ሁሉ ንብረት ያንተ ይሁን።" ብሎት ከአካባቢው ጠፋ። በመቃብር ሥፍራ ለሦስት ቀናት ያለ ምግብ ጸልዮ የእግዚአብሔር መልአክ ሰው ወደ ማይደርስበት በርሃ ወሰደው።
በዚያም ምንጭ ፈለቀችለት። እየጾመ ይጸልይ ይሰግድ ገባ። ሁሌ ማታ ግማሽ ሕብስት ከሰማይ እየወረደለት ቅዳሜና እሑድ መላእክት እያቆረቡት ለሰማንያ ዓመታት ኖረ። (አንዳንድ ምንጮች ግን ለዘጠና ዓመታት ይላሉ።) ከቅዱስ እንጦንስ ጋር የተገናኙትም ከዚህ በኋላ ነው።
ከቅዱስ እንጦንስ ጋር በነበራቸው የሁለት ቀናት ቆይታም ቅዱስ ጳውሊ ብዙ ትንቢቶችን ተናግሯል። በዚህች ቀን ሲያርፍም መቃብሩን አናብስቱ ቆፍረዋል። ቅዱስ እንጦንስም በክብር ቀብሮታል። ለሰማንያ ዓመታት የለበሳት የዘንባባ ልብሱም ሙት አስነስታለች።
††† ጻድቅ፣ ቡሩክ፣ ቀዳሚው ገዳማዊ፣ መላእክትን የመሰለና የባሕታውያን ሁሉ አባት ለተባለ ለቅዱስ ጳውሊ ክብር ይገባል!
††† አባ ለንጊኖስ †††
††† ጻድቁ ከኪልቅያ እስከ ሶርያ ከሶርያ እስከ ግብጽ ድረስ በተጋድሎ የተጓዙ አባት ናቸው። በአምስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽም የደብረ ዝጋግ (ግብጽ፤ እስክንድርያ) አበ ምኔት ሆነው አገልግለዋል።
ሙታንን አስነስተው ሃይማኖታቸውን ጠብቀው ብዙ ተአምራትን ሠርተው በዚህች ቀን ዐርፈዋል። ከድንቅ ነገራቸው ሰይጣን የእርሳቸውን የምንኩስና ቆብ ዐይቶ ደንግጦ መሸሹን እንጠቅሳለን።
"ኀበ ኢኀሎከ ሶበ ቆብዓከ ርዕየ
ሰይጣን ተኃፊሮ እፎኑመ ጐየ።" እንዲል።
(አርኬ)
††† አምላክ በበረከታቸው ይባርከን።
የካቲት ፪ ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
፩.ቅዱስ አባ ጳውሊ ገዳማዊ (የባሕታውያን ሁሉ አባት)
፪.ቅዱስ አባ ለንጊኖስ ሊቀ ምኔት (ደብረ ዝጋግ)
፫.ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ
††† ወርኀዊ በዓላት
፩.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት
፪.ቅዱስ ታዴዎስ ሐዋርያ
፫.ቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ (የሃይማኖት ጠበቃ)
፬.ቅዱስ ኢዮብ ጻድቅ
፭.ቅዱስ አቤል ጻድቅ
፮.አባ ሕርያቆስ ዘሐገረ ብሕንሳ
††† "የሚበልጠውን ትንሣኤ እንዲያገኙ እስከ ሞት ድረስ ተደበደቡ። ሌሎችም መዘበቻ በመሆንና በመገረፍ ከዚህም በላይ በእስራትና በወኅኒ ተፈተኑ። በድንጋይ ተወግረው ሞቱ። ተፈተኑ፤ በመጋዝ ተሰነጠቁ፤ በሰይፍ ተገድለው ሞቱ። ሁሉን እያጡ፣ መከራን እየተቀበሉ፣ እየተጨነቁ የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው ዞሩ። ዓለም አልተገባቸውምና በምድረ በዳና በተራራ በዋሻና በምድር ጉድጓድ ተቅበዘበዙ።" †††
(ዕብ ፲፩፥፴፭-፴፰)
††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
ቃል ሂወት ያሰማልን እግዚአብሔር ቸር ነው
🤲
😭
በረከታቸዉ ይደርብን የቅዱሳን አባቶቻችን ምልጃ አይለየን
አሜን አሜን አሜን በረከታችሁይደርብን
የፃድቃን አባቶቻችን በረከት ይደርብን ልኡል እግዚአብሔር አተ ይቅር በለን የቀና መገድም ምራን
ኣምላክ ቅዱሳን የቅዱሳን በረከታቸው ያሳድርብን
❤""ውይ እንዴት ደስ ይላል የፃድቃን በረከታቸው ይደርብን❤❤❤
ቃል ህይወት ያሰማልን አሜን አሜን አሜን
አሜን አሜን አሜን
አሜን አሜን አሜን❤❤
በረከታቸው ይድረሰን😾🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭
❤❤❤❤
የቅዱስ እንጦንስ እና የአባ ጳውሊ ጸሎትና ልመናቸው ረድኤት በረከታቸው ይደርብን አሜን😢❤❤❤❤
እግዚአብሔር ይመስገን የአባቶቻች በረከታቸው እረደእታቸውይደርብን🤲🤲🙏
እግዚአብሔር አምልክ የፓዉሊን ልብ ይስጠን ስለ ቅድሳን ብለክ ማረን አቤቱ ቅድስ ቃልክንም ለሚያስሙን እድሜና ጤኔ ሰጣቸዉ❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤
አሜን አሜን እግዚአብሔር ከቅዳሳን አባ እንጦንስ እና ከአባ ጳውሊ በረከታችው ጸሎት ለመናቸው ይድረሰን
የቅዱሳኑ በረከት ይደርብን
የአባ ጰዉሊ የአባ እንጦስ እድሁም አብረዉ በሉትም መናኮሳት ረደኤት በረከት ምልጃን ፁሎት አይለየን አሜን አሜን አሜን🙏🙏🙏
እግዚአብሔር ይመስገን አሜን አሜን አሜን ቃለ ሕይዎት ያሠማልን አባታችን በረከትሕ ይደርብን🙏🙏🙏⛪️⛪️⛪️🕯🕯🕯:
የቅዱስ አባ ጳውሊ እና የአባ እንጦስ በረከታቸው እና ረድኤታቸው አይለየን አሜን!!!
በጣም መሳጭ ነው እግዛብሄር ይመስገን የአባቶቻችን በረከት አይለየን አሜን፫
አሜን የአባታችን የአባ ጳዉሊ እና የአባ እንጦንስ በረከት ይደርብን 🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
ቃለ ህይወት ቃለ በረከትን ያሠማልን ነአባቶቻችን በረከታቸው ይደርብን 🙏ለተረጎማችሁልን የህንን የህይወት እንጀራን ለመገባችሁን ወንድም እህቶቼ የዘለዓለም አምላክ የመንግስቱ ወራሽ ያርግልን 🙏በእውነት ሁሌ ባየው የማልጠገበው የእምነት ተጋድሎ ነው😢አግዚአብሔር ከክፉ ሁሉ ይጠብቀን የመንግስቱም ወራሽ ያርገን መንገድንከሚያስቱ ስጋ ለበስ ጥላቶች ያድነን🙏❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤
የአባቶቻችን የሀዋርያት በረከታቸዉ ድል የማትነሳ እረዴታቸዉ ጥርጥር የሌለባት ተዋህዶ ሀይማኖታቸዉ ከእኛ ጋር ትሁን ለዘለአለም አሜን::❤❤❤
በረከታችሁ ይደርብን
በዉነት የቅዱሳን ልመናቸዉ ፆለታቸዉ ፅናታቸዉ በኛላይም ይደርብን ቃለሂወትን ያሠማልን ፫ የኛንም ልቦናችንን አብርቶ ይህንንየሠማነዉን ቃል በልቦናችን ያሣድርብር 👏🙏😢😢
እግዚአብሔር ይመሥገን የቅዱሳን ፀሎታቸዉ በረከታቸዉ እንባቸዉ አይለየን አሜን አሜን አሜን
አሜን።የታላቁ አባታችን አባ ጳዉሊ በረከቱ ይደርብን🙏🙏🙏።
አሜን የአባ ጳውሊ የአባ እንጦስ እድሁም አብረው ያሉትም መነኮሳት ረደት በረከት ምልጃና ፀሎት አይለየን አሜን💚💚💚💛💛💛❤❤❤😢😢
Amen Amen Amen
የአባ ጳዉሊ እና የአባ እንጦስ የእነዚህ ቅድሳን አባቶች በረከታቸዉ ይደርብን አሜን
ስለቅዱስ ቃሉ የቃሉ ባለቤት ልዑል እግዚአብሔር ይመስገን❤
የቅዱሳን በረከታቸዉ ይደርብን 👏👏
በህይወት መንፈሳው ፍልም አይቼ እንደ ዛሬ አልቅሻ አላቅም የአባቶቻችን በረከት አማላድነት አይለየን👏👏👏👏👏
ግብፃዊዋ ማርያም ብለሽ እይ እሱም ያስተምራል
አሜን፫የአበታችን በረከት ይደርብን🙏🌿🙏🌿👏
እግዚኘብሔር ይመስገን አቤቱ ጌታ ሆይ 😢😢😢😢😢😢😢😢በቅዱሳን ባባቶቻችን ጸሎት ልመና ማርን ይቅር በለን በረከታቸዉ ይደርብን🥀🥀🥀🥀🥀
የቅዱስ አባ እንጦንስ ቅዱስ አባ ጻውሊስ በረከታቸው ይደርብን በፀሎታቸው ይማረን አሜን አሜን አሜን 🤲🤲🤲
አሜን አሜን አሜን የቅዱሳኑ በረከት ይደርብን🤲🤲🤲እኔ ማነኝና ጎበኜህኝ አምላኬ ሆይ ክብር ምስጋና ለአንተ ይሁን🤲🤲🤲
እግዚአብሔር ይመስገን የቅሳን በረከት ይደርብን አሜን ❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤
የአባታችን በረከትይደርብን ለዘላለሙጨ አሜን አሜን አሜን❤🤲🤲🤲🤲👏👏👏👏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
በእውነቱ ክርስትና እንደዚ ናት ተመስጌን አምላኬ አብነት አባቶችን ስለሰጠኸን የቅዱሳን በረከት ምልጃ እና ፀሎት አይለየን አሜን
በእውነት እንደ አባ ጿውሊ መሆን ፈለኩ 😭😭👏👏👏
የቅዱሳን እረደየትና በረከት ይደርብን
እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን የቅዱሳን የሰማዕታት በረከት ረድኤታቸው ይደርብን ይባርከን ቃለ ህይወትን ያሰማልን ኦርቶዶክስ ለዘለዓለም ትኑር ❤❤ ተመስገን
የቁዱሳን በረከታአቸው ይደርብን አሜን 🤲❤
አሜን አሜን አሜን እግዛቢሄር የተመሰገነ ይሁን የፃዲቅ በረከት ይደርብን❤❤❤
የቅድሳን በረከት እረዴታቸው በእኛ በደካሞች ላይ የደርብን አሜን አሜን አመን
እግዚአብሔር ይመስገን ለአባቶቻችን ቃለ ህይወት ያሰማልን❤❤❤❤❤
የአባ ጳውሊ እና የአባ ኢጦስ በረከታችው ይደርብን😢😢😢😢
ቃል ህይዉት ያሰማልን በረኩታችዉ ይደርብን አባቶቻችን ፫ ❤
የቅዱሳንአባቶቻቺን እርዴት በርከታቸው ይደርቡን
እግዚአብሔር ይመስገን የአባቶቻችን በረከት አይለየን አሜን ፫ 🙏
አሜን አሜን አሜንበረከታቸው ከኛ ጋር ይደር እግዚአብሔር የተመሰገነ ነው::
ስለ ቅዱስ ቃሉ የቃሉ ባሌቤት የቅዱሳን አምላክ ልዑል እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን
የቅዱስ ጳውሊ በረከት ረድኤት ይደርብን አሜን
አሜን ቃለሂወት የስመአና
የቅዱሳኑ በረከታቸው ይደርብን አሜን
ኦርቶዶክስ መሆን መመረጥ ነው ።
እግዚአብሔር ይመስገን ይሄን የተቀደሰ የአባቶቻችንን ገድል እዳይ ስለፈቀደልኝ💖⛪💖⛪💖⛪🌹🎉🎉🎉🎉🎉💖⛪💖🤲🤲🤲🤲🤲🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏አሜን አሜን አሜን
የባቶቻችን በረከታቸዉ ከኛጋር ይሁልን ኣሜን ፫ ቃለሂዉት ያሰማልን
አሜን፫
የቅዱስ ኣባ ጳውሊ እና ቅዱስ እንጦስ በረከታቸው ይደርብን
በረከታቹ ይድረሰን /ኝ ቅዱሳን አባቶቼ🙏❤🙏😘🙏❤🙏
እግዚአብሔር ይመስገን የቅዱሳኑ በረከት ይደርብን🤲🤲🤲
ቃለሒወት ያሰማልን በረክታቼው ይደርብን
የቅዱሳኑ በረከት በኛ ላይ ይደርብን ❤
እግዚአብሔር ይመስገን የቅዱሳን የአባቶቻችን ፆሎታቸው በረከታቸው ይደርብን ቃለ ህይወት ያሰማልን እሰይ እሰይ እሰይ እንደ ዛሬ ቀን በጣም ደስ ይላል ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መሆን እኮራለው
We
Amen Amen Amen
@@alemneshalemu1666 Ĺp⁰
@@alemneshalemu1666❤
እውነት ነው ቃለህይወትን ያሰማልን 💕🙏💕
አሜን አሜን የቅዱሳን በረከት ይደርብን
አሜን አሜን አሜን የቅዱሳን አባቶቻችን በረከታቸው ምልጃ ጥበቃቸው አይለየን ቃለ ህይወት ያሰማልን አቤቱ ጌታሆይ በመልካሙ መንገድህ ምራን እኛንም በሀይማኖት በምግባር አፅናን🤲🤲🤲🤲🤲❤❤❤
ኣሜን ኣሜን ኣሜን ቃለ ህይወት የስመዐልና በረከቶምን ረድኤቶምን ናይ ቅዱሳን ኣቦታትና ምስ ኩላትና ህዝበ ክርስትያን ይኹን ኣሜን💒
አሜን አሜን አሜን የአባ ጻዉሊ እና የአባ እንጦንስ በረከታቸዉ እረድኤታቸዉ ከኔ ከሀጢያተኛዋ ከህተ ወልድ ጋራ ይኑር እዲሁም ከእናቴ እህተ ማርያም ጋራ ይኑር
አሜን፫ ቃልህይወትን አሜንአሜንአሜንየአባጻዉሊእናየአባእንጦንስበረከታቸዉእረድኤታቸዉከኔከሀጢያተኛዋከህተወልድጋራይኑርእዲሁምከእናቴእህተማርያምጋራይኑርአሜን፫ቃልህይወትን ያሰማልን
የቅዱሳኑ በረከት ለተዋህዶ ወገኞቼ ይድረሰን ሀይማኖታችንና አገራችንን ይባርኩልን እነሱ ጌታ የመረጣቸው ሰለሆኑ ምድራችንን ይባርኩልን ለእኛ ለምናምናቸው አሜን።
የቅዱሳን በረከታቸዉ ከሁላችን ይሁን❤❤❤
ጌታሆይ ይህን የተባረከ የተቀደሰውን ቅዱሱን ቃልህን በቅዱሳኖችህ ተጋድሎ ቅድስና ስለአሰማኸኝ አመሰግንሀለው ጌታሆይ እኔን ደካማዋን ባሪያህን በቅዱሳን በረከት ባርከኝ አይነ ልቦናዬንም አብራልኝ😭😭😭😭😭😭
የአባቶቻችን በረከት ከኛጋ ይሁንልን ❤❤❤
በጣም የምወደው ታሪክ የአባታችን ጳውሎ ታሪክ አይች አልጠግበውም በእውነት እግዚአብሔር በረከታችሁ ይድርብን
የአባቶቻችን በረከታቸዉ ይደርብን 🙏🙏🙏
አሜን አሜን አሜን በረከታቸው ይደርብን እሱን ያመነ መቼም አይወድቅም
እህቴ ይቱቤን አቀይሪብኝ በእመ አምላክ ስም።
እግዚአብሔር ይመሰገን አሜን የቅዱሳን አባቶች ጸሎታቸው በረከታቸው ይደርብን አሜን አሜን አሜን⛪⛪⛪🕊🕊🕊🌾🌾🌾🌿🌿🌿
ናይ ኣባ ጳውሊ በረከቶምን ጸሎቶምን ምስ ኩላትና ህዝቤ ክርስታይን ይኩን ሙቁራተይ💞💞💞
አሜን አሜን አሜን
የቅዱሳን ጸሎት
በረከታቸው ይደርብን🙏
የአባቶቻቺን ፀሎ የፃድቃን ሠማእታት ምሎጃ አይለየን እንደበደላቺን ሳይሆን በነሡ ፀሎት ይማረን🙏🙏🙏🙏🙏
በስመ አብ ግሩምና ድንቅ ነው የአባቶቻችን በረከት ይድረሰን አሜን አሜን አሜን
ቃሐ በረከትን ቃለ ህይወትን ያሰማልን በረከታቸው ይደርብን አባቶቻችን አሜን👏👏👏
በጣም፡ደስ፡የሚል፡በታሬካዊ፡የተመሠረተ
የክርስቶስ፡አገልጋዮች፡ትምሕርተ፡ታሬክ
አብዝቶ፣አብዝቶ፣አብዝቶ፣ይባርካችሁ።
የመናኞች፤የፃድቃን፤የሰማዕታት ረድኤት በረከታቸው ምልጃቸው ለኢትዮጵያ ሰላሙን ያውርድልን 🥰🤲🙏
የቅዱሳን አታቺን በረከት ይዋልና ይደርብን::
ናይ ቁዱሳት አቦታትና ፀለቶም በረከቶምን ቃልኪዳኖምን ንኣና ንሓጥኣተኛ ታት ይኹን ኣሜን ኣሜን ኣሜን🙏
የአባቶቻችን በረከት ይደርብን 🙏🙏🙏
አቤቱ ጌታ ሆይ ለንስሀ ሞት አብቃኝ አባት ሆይ የቅድሳን አባቶቻችን በረከታቸው ይደርብን አሜንን
አይቼ የማልግበዉ ፊልም የአባቶቻችን በረከት ረድኤት ይደርብን ኣሜን🤲🤲🤲
በረከታቸዉ ይደርብን ቃልሂወት
ያሰማልን
እግዚአብሔር አማላክ የፖውሊን ልብ ይስጠን ስለ ቅድሳን ብለክ ማረን አቤቱ ቅድስ ቃልክንም ለሚያስሙን እድሜና ጤና ስጣቸው
እግዚአብሔር ሆይ እንዴት ደስ የሚል ትምህርት ነው ልብን ይማርካል ተመስገን በረከታቸው ይደርብን
አሰይይይ በረክትች ጾሎትች ናይ አቦታችንን ያድረሰኝ አሜን አሜን አሜን🤲🤲🤲🤲
ቃለ ሂወት የስመዓልና የቅዱሳን የአባቶቻችን ጸሎታቸው በርከታቸው ይድርብን❤❤
የቅዱሳን አምላክ ሆይ እኛን በደለኞቹን ማረን የአባቶቻችን በረከት አይለየን
ብጣም ደስ ይሚል ልብ ይማርካ ትምህረት ነው ይቁደሳን ብረክታችው በኒ በሃጤኝዋ ይደር አሜን እግዛኣቤሔር ይመሰገን 🙏🙏🙏🙏
🙏🙏🙏❤❤❤
እግዚአብሔር ይመሠገን የቅዱሳን አባቶቻችን በርከት አይለየን በእውነት እሆን ቦታ በማየቴ እድለኝ ነኝ
ቃለ ሂወት ያሰማልን በረከታቸው ይደርብን አባቶቻችን መታደል ነው። 😢😢😢
የቅዱሣን በረከታ ቸው ይደርብን
አሜን አሜን አሜን ❤❤❤❤❤ በረከታችሁ ይደር ብን🙏🙏🙏🙏🙏
አሜን በረከታቸው ይድረሰን ለምታሰጋጁ ለምትልኩልንም ሁሉ ዎጋ ሰማያዊ ይስጥልን አሜን
"የጳውሊ አምላክ ሀገራችንን ሠላም ያድርግልን "
እናንተም እግዚያብሄር ይባርካቹ! ሁሌ ስሰማዉ ያረጋጋኛል!!!
የባቴቻችን በረከት በሁላችላይደር አሜን አሜን አሜን❤❤❤❤
የተራቡትን ወገኞቼን የእነ አባ እንጦሰ አምላክ በረከቱን ያድላቸው ያጥግባቸው ከመራብ ከመጠማት ሥጋቸውን ያጥግባቸው ጌታ በሙሉ እጁ ያሰባቸው ።
እግዛብሄር ይመስገን የቅዱሳን የአባቶቻችን ፆሎታቸው በረከታቸው ይደረብብን ቃለሂወት ያሰማልን ❤❤❤❤❤አሜን (፫)
በረከታቸው አይለየን❤❤❤
የአባቶቻችን በረከታቸው ክእኘ ጋር ይሁንልን ፀጋውን ያብዛልን አሜን ይደረግልን🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
አሜን ተመስገን አምላኬ ሆይ እሂን እዳይ ስለፈቀድክልይ ክብር ምስጋና ይግባህ አሜን
አሜን አሜን አሜን የቅዱሳኖች ቨረከት ይደርብን
እግዚአብሔር አምላክ ሥለቅዱሳኑ በረከት ይባርከን
የቅዱሳን አባቶቻችን በረከታቸው ይደርብን